የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት

ኢተምድ የሚለው ምህፃረ ቃል ፡ የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት” ይወክላል፡፡ ኢተምድ በጥር ወር 2003ዓ.ም በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 196/2003 በፌደራል ደረጃ የመንግስት የልማት ድርጅት ሆኖ የተስማሚነት ምዘና አገልግሎቶችን ለመስጠት ተቋቁሟል፡፡ የድርጅቱ ተቆጣጣሪ ባለስልጣን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ነው፡፡ ኢተምድ በዋነኝነት የተስማሚነት ምዘና አገልግሎቶች ማለትም የላብራቶር ፍተሻ፣ የኢንስፔክሽንና የሰርቲፊኬሽን አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን በስሩ ከ200 በላይ ሰራተኞችን ይዞ 8ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች በመላው ሀገሪቱ በማደራጀት እየሰራ የሚገኝ ድርጅት ነው፡፡

አድራሻ

ገርጂ

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ የአገሪቱን ግብርና በገበያ ላይ ወደተመሰረተ የአመራረት ስርዓት ለማሸጋገር እንዲሁም አነስተኛ የግብርና አምራቾች በገበያው ላይ ያላቸውን ተሳትፎ ፍትሃዊ ለማድረግ በማሰብ ቀልጣፋ፣ ስርአት ያለውና ወጥነት ያለው የግብርና ምርቶች የሚገበያዩበት  የገበያ ስርዓት ለመፍጠር በኢትዮጵያ ምርት ገበያ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 550/2007 መሰረት በ2000 ዓ.ም የተቋቋመ ድርጅት ነው፡፡

አድራሻ

ሜክሲኮ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ አክሬዲቴሽን ጽ/ቤት

የራሱ ሕጋዊ ስብዕና ያለው ራሱን የቻለ የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ ቤት ሆኖ ተቋቋመ። ተልእኮ እንደ ሶስተኛ ወገን ዕውቅና ፣ የተስማሚነት ግምገማ አካላት (ሲኤቢኤስ) እንደ ሙከራ ፣ መመዘኛዎች ፣ የምስክር ወረቀቶች ወይም ምርመራዎች ያሉ የተወሰኑ እንቅስቃሴዎችን ማከናወን ዕውቅና መስጠት ነው።

አድራሻ

ቦሌ ክፍለከተማ መገናኛ ከአምቼ አጠገብ