"ዲጂታል ትራንስፎርሜሽንን ማሳደግ የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥን ለማሳለጥና ለስራ ዕድል ፈጣራ ጉልህ ሚና አለው" ፡- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

"ዲጂታል ትራንስፎርሜሽንን ማሳደግ የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥን ለማሳለጥና ለስራ ዕድል ፈጣራ ጉልህ ሚና አለው" ፡- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ==================== አዲስ አበባ 14/09/2016ዓ.ም(ንቀትሚ) ዲጂታል ትራንስፎርሜሽንን ማሳደግ የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥን ለማሳለጥ፣ ለማህበራዊ ተሳትፎና ለስራ ዕድል ፈጣራ ፋይዳው የጎላ ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ። የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ባዘጋጀው ስትራይድ ኢትዮጵያ ኤክስፖ (STRIDE Ethiopia 2024 Expo) ላይ ትኩረቱን ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ላይ ያደረገ ውይይት ተካሄዷል፡፡ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በውይይቱ እንደገለጹት፤ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ኢኮኖሚን ለመገንባት፣ ለማህበራዊ ተሳትፎ፣ ለስራ ዕድል ፈጠራና የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥን ለማሳለጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደርጋል ብለዋል፡፡ ዲጂታል 2025ን ዕውን ለማድረግ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ካውንስል ተቋቁሞ እየተሰራ መሆኑን ገልጸው፤ ይህም ወጪ ቆጣቢ አሰራርን ለመከተል፣ ቅንጅታዊ አሰራርንና የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እድገትን ለማፈጠን ያግዛል ብለዋል። የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ስትራይድ ኢትዮጵያ ኤክስፖ (STRIDE Ethiopia Expo 2024) ተሳታፊ በመሆን የኦንላይን የንግድ ምገባና ፈቃድ አገልግሎት አሰጣጡን ለጎብኝዎች እያስተዋወቀ ይገኛል፡፡ አገልግሎቱ በሁሉም ክልሎቸና ከተማ አስተዳደሮች ከ 2013ዓ.ም ላይ ተግባራዊ የተደረገ መሆኑንና አስካሁን ከ1.6 ሚሊዮን በላይ ተጠቃሚዎች(users) የተመዘገቡ ሲሆን እስካሁን ከ2.2 ሚሊዮን በላይ አገልግሎቶች በኦንላይን የተሰጡ መሆኑን አቶ ፀጋው በለጠ በሚኒስቴር መ/ቤቱ የኢንፎርሜሽንና ኮሙኒኬሽን ስራ አስፈፃሚ ገልፀዋል፡፡

Share this Post