በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በምርቶች ላይ ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ ባደረጉ ህገ-ወጥ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ ተወሰደ

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በምርቶች ላይ ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ ባደረጉ ህገ-ወጥ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ ተወሰደ =================================== በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በምርቶች ላይ ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ ባደረጉ 451 ህገ-ወጥ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ መውሰዱን የክልሉ ንግድና ኢንቨስትመንት ቢሮ አስታውቋል፡፡ ቢሮው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ሪፎርሙን ተከትሎ የሚፈጸሙ ህገ-ወጥ ተግባራትን ለመቆጣጠር እየሰራ መሆኑን ገልጿል፡፡ በክልሉ ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉ ነጋዴዎች ላይ እየተወሰደ ያለው እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም የቢሮው ኃላፊ አቶ ተመስገን ከበደ ተናግረዋል፡፡ ኃላፊው ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት የንግድ አሻጥር የሚያደርጉ ነጋዴዎች፤ ምርት እንደሌለ አድርገው በማኀበራዊ ሚዲያ የሚያሰራጩት ወሬ መሠረተ ቢስ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ “ክልሉን እየጎዳ ያለው ያለአግባብ ዋጋ መጨመር፣ ምርት መደበቅ እና ምርት ማሸሽ ነው” ያሉት አቶ ተመስገን ከበደ፤ በህገ-ወጥ ተግባራት ላይ የተሰማሩ ነጋዴዎች ላይ ከማስጠንቀቂያ እስከ ሱቅ ማሸግ እና በህግ መጠየቅ የደረሰ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን አመላክተዋል፡፡ በክልሉ በንግድ ስርዓቱ ላይ የሚስተዋለውን ህገ-ወጥ አሰራር ለመከላከል የተቋቋመው ግብረ-ኃይል ወደ ስራ መገባቱንም አስታውቀዋል፡፡

Share this Post