በዓሉን ምክንያት በማድረግ በቁም እንስሳት ግብይቱ የተጋነነ የዋጋ ጭማሪ አለመኖሩን ነጋዴዎችና ገዥዎች ገለጹ፡

በዓሉን ምክንያት በማድረግ በቁም እንስሳት ግብይቱ የተጋነነ የዋጋ ጭማሪ አለመኖሩን ነጋዴዎችና ገዥዎች ገለጹ፡፡ ========================= አዲስ አበባ 25/04/2016ዓ.ም (ንቀትሚ) በቄራ የቁም እንስሳት የገበያ ማዕከል የተሻለ አቅርቦትና በመኖሩ የተረጋጋ ግብይት እየተከናወነ እንደሚገኝ በቄራ የቁም እንስሳት ገበያ ማዕከል የቁም እንስሳት ሽኝት ባለሙያ አቶ ኤፍሬም ወልዴ ገልጸዋል፡፡ በዓልን አስልክቶ የዋጋ ጭማሪ ቢታይም አቅርቦቱ ጥሩ በመሆኑ ሁሉም እንደአቅሙ ከ35ሽ እስከ 200 ሺ ብር ድረስ ግብይት እንደሚካድ አቶ ኤፍሬም ተናግረዋል፡፡ የቄራ ከብት ገበያ ነጋዴዎች ማህበር ሰብሳቢ አቶ ሙሉጌታ ወረደ አቅርቦቱ ጥሩ መሆኑን በመጠቆም ከሀገሪቱ ወቅታዊ ነባራዊ ሁኔታ አንፃር ዋጋው ጥሩ እንደሆነና ከመደበኛ ገበያው ጋር ሲነፃፀር ብዙ እንዳልጨመረ ጠቅሰዋል፡፡ አቶ ሙሉጌታ አክለውም ዝቅተኛ ከ25ሽ ብር ጀምሮ እየተሸጠ እንደሚገኝና መካከለኛ ከብት ከ70-80 ሺህ እንዲሁም ከፍተኛ እስከ 200ሺ ብር እየተገበያየ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡ እንዲሁም በአቃቂ የቁም እንስሳት ግብይት ማዕከል የተሻለ አቅርቦት እንዳለ ባደረግነው ቅኝት የተመለከትን ሲሆን በአዲስ አበባ በሚገኙ የቁም እንስሳት የግብይት ማዕከላት በመገኘት ህብረተሰቡ በተረጋጋ መንፈንስ ግብይት እዲያካሂድም የማዕከላቱ ኃላፊዎች መልዕክት አስተላፈዋል፡፡

Share this Post