ለኢትዮጵያ የብልፅግና ጉዞ ስኬት አገልጋይና ስልጡን ስቪል ሰርቪስ መገንባት ይገባል።

ለኢትዮጵያ የብልፅግና ጉዞ ስኬት አገልጋይና ስልጡን ስቪል ሰርቪስ መገንባት ይገባል። ===================== አዲስ አበባ 29/05/2016ዓ.ም (ንቀትሚ) በኢትዮጵያ እየተካሄደ የሚገኘውን ሀገራዊ ለውጥ መሸከም የሚችል ገለልተኛና አካታች ሲቪል ሰርቪስ መገንባት ወሳኝ ነው ሲሉ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የንግድ ስርዓትና ላይሰንሲንግ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ፍሰሃ ይታገሱ ተናግረዋል፡፡ የሚኒስቴር መ/ቤቱ አመራሮችና ሰራተኞች ከትናንት ጀምሮ እየወሰዱት ያለው ስልጠና ዛሬም የቀጠለ ሲሆን አገልጋይና ስልጡን ሲቪል ሰርቪስ ለኢትዮጵያ ብልፅግና በሚል ርእስ የተዘጋጀው የውይይት ሰነድ በሚኒስትር ዴኤታው አቶ ፍሰሃ ይታገሱ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡ በሰነዱ ላይ የተለያዩ ሀሳቦች ተነስተው ውይይት የተደረገበት ሲሆን አለም በፈጣን የለውጥ ሂደት ላይ መሆኖን ተከትሎ እኛም እንደ ሀገር የተሰጠንን ተልዕኮ በተሰማራንበት መስክ ዘመኑን የሚመጥን አገልግሎት መስጠት ይጠበቅብናል ያሉት ደግም የጥራት መሰረተ ልማትና ማረጋገጫ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ እንዳለው መኮንን ናቸው።

Share this Post