የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አመራሮችና ሰራተኞች በሀገራዊና ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አካሄዱ፡፡

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አመራሮችና ሰራተኞች በሀገራዊና ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አካሄዱ፡፡ ==================== አዲስ አበባ 28/05/2016(ንቀትሚ) ከ”እዳ ወደ ምንዳ” በሚል መሪ ሃሳብ እንደ ሀገር በተዘጋጀው የውይይት ሰነድ ላይ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አመራሮችና ሰራተኞች ውይይት እያካሄዱ ይገኛሉ፡፡ የውይይት አላማው ሰራተኛው በሀገራዊና ክልላዊ የፖለቲካ፣ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም የሰላም ሁኔታ ላይ በመወያየትና በመመካከር የተሻለ ግንዛቤ በመፍጠር ሁሉም የመንግስት ሰራተኛ ለተጀመረው የብልፅግና ጉዞ የበኩሉን ሚና እንዲወጣ ለማድረግ ነው ሲሉ የንግድ ስርዓትና ላይሰንሲንግ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ፍሰሃ ይታገሱ ገልፀዋል፡፡ ውይይቱ በመጀመርያ ቀን ውሎው ሀብት የመፍጠር ጉዟችን፣ እያጋጠሙን ያሉ ተግዳሮቶችና ቀጣይ አቅጣጫዎች በሚል ርእስ የተዘጋጀ የውይይት መነሻ ሰነድ በንግድ ትስስርና ወጪ ንግድ ፕሮሞሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ካሳሁን ጎፌ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ ገብረመስቀል ጫላ ኢትዮጵያ እያጋጠማት ያለውን ፈተናዎች እየተጋፈጠች ተግዳሮቶችን ተቋቁማ በለውጥ ጎዳና ወደ ብልጽግና ለመሸጋገር እያደረገች ባለው ጥረት ሁሉም አካላት በመደገፍ የበኩሉን ሚና ሊወጣ ይገባል ብለዋል፡፡ ውይይቱ በነገው እለትም አገልጋይና ስልጡን ሲቪል ሰርቪስ ለኢትዮጵያ ብልፅግና በሚል ርእስ የሚቀጥል ይሆናል፡፡

Share this Post