በጥራት ፖሊሲ ትግበራ ላይ አውደ ጥናት እየተካሄደ ነው፡፡

በጥራት ፖሊሲ ትግበራ ላይ አውደ ጥናት እየተካሄደ ነው፡፡ ==================== አዲስ አበባ 05/06/2016ዓ.ም (ንቀትሚ) የንግድና ቀጣናዊ ትስሰር ሚኒስቴር የጥራት መሠረተ ልማት ዘርፍ በብሪትሽ ስታንዳርድ ኢንስቲትዩት ድጋፍ በጥራት ፖሊሲ ትግበራ ላይ አውደ ጥናት እያካሄደ ይገኛል፡፡ በአውደ ጥናቱ የመጀመሪያ ቀን ከአግሮ ፕሮሰሲንግ ዘርፍ ለተወከሉ የግሉ ዘርፍ እና የመንግስት ባለድርሻ አካላት ስለ ጥራት ፖሊሲ ምንነት፣ አስፈላጊነትና ጠቀሜታ ዙርያ ሰነድ ቀርቦ ማብራሪያ የተሠጠ ሲሆን በትግበራ ሂደቱ እና በዘርፉ ያሉ ክፍተቶች ላይ ውይይት ተከናውናል፡፡ የውይይት መድረኩ ከጨርቃ ጨርቅ ዘርፍ ባለድርሻ አካላት እንዲሁም ከቆዳ ዘርፍ ባለድርሻ አካለት ጋር የሚደረገው ውይይት በቀጣይ ቀናት እንደሚቀጥል ይጠበቃል፡፡

Share this Post