የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጠና ስምምነት ትግበራ ማፋጠን ላይ ያተኮረ ስልጠና እየተሰጠ ነው

የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጠና ስምምነት ትግበራ ማፋጠን ላይ ያተኮረ ስልጠና እየተሰጠ ነው ================== አዲስ አበባ 12/06/2016 (ንቀትሚ)የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጠና ስምምነት ትግበራን ማፋጠን እና የአፍሪካ የንግድ እና የኢኮኖሚ ትስስርን ማሳደግ በሚል መሪ ሃሳብ ለአምባሳደሮች እና ለዲፕሎማቶች ስልጠና እየተሰጠ ነው። በአዲስ አበባ የአፍሪካ ህብረት ዋና መስሪያ ቤት ውስጥ እየተሰጠ ባለው ስልጠና አምባሳደሮች፣ የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ርዕሰ አካዳሚ ዛዲግ አብርሃ እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል። ስልጠናው በአፍሪካ ሀገራት መካከል የሚደረገውን የግብይት መጠን እና የንግድ ትስስር ለማሳደግ ያለመ ሲሆን ከዛሬ ጀምሮ ለሁለት ቀናት እንደሚሰጥ ተመላክቷል ሲል ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል፡፡

Share this Post