የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ ገብረመስቀል ጫላ ከዩናይትድ ኪንግደም የንግድ ፖሊሲ ሚኒስትር ዴኤታ ግሪጎሪ ዊሊያም ጋር ተነጋገሩ።

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ ገብረመስቀል ጫላ ከዩናይትድ ኪንግደም የንግድ ፖሊሲ ሚኒስትር ዴኤታ ግሪጎሪ ዊሊያም ጋር ተነጋገሩ። ======================= አዲስ አበባ 20/06/2016ዓ.ም (የንቀትሚ) ከ13ኛው የዓለም ንግድ ድርጅት የሚኒስትሮች ጉባኤ ጎን ለጎን አቶ ገብረመስቀል ጫላ የተመራ የልዑካን ቡድን ከዩናይትድ ኪንግደም ልዑክ ጋር በእድገት ወደ-ኋላ ለቀሩ ሃገራት በተዘጋጀው ውይይት እና የሁለትዮሽ ውይይት አካሂዷል፡፡ በውይይቱ ሚኒስትሩ የኢትዮጵያን የአባልነት የድርድር ሂደት ለማገዝ የእንግሊዝ መንግስት በሚሰጠው የቴክኒካል ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡ እንደ ኢትየጵያ ላሉ በእድገት ወደ-ኋላ ለቀሩ ሃገራትን ተጠቃሚነትን ለማስጠበቅ የአለም አቀፍ የገበያ ፍትሃዊነትን እና ተደራሽነት ማስጠበቅ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል። በዋናነት ታሪፍ ያልሆኑ የንግድ መሰናክሎች በኢኮኖሚ ዝቅተኛ ለሆኑ ሃገራት ተወወዳደሪነት ላይ ጫና እንደሚሆንባቸው ያነሱት ሚኒስትሩ ይህንን ጫና ለመቀልበስ ያደጉ ሃገራት ድጋፍ የሚኖረው ሚና ከፍተኛ ነው ብለዋል። ሃገራችን የባለ-ብዙ ወገን የገበያ ስርዓት አካል ለመሆን በምታደርገው የድርድር ሂደትም ሆነ ከአባልነት በኋላ ተጠቃሚነትን ለማሳደግ ቀጣይነት ያለው ተቋማዊ የአቅም ግንባታ ስራዎች እና የመሰረተ ልማትን ለማሻሻል ከእንግሊዝ መንግስት የሚሰጠን ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ሚኒስትሩ ጠይቀዋል።

Share this Post