”የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ተአማኒነት ግብረ ሃይል”ተቋቋመ።

”የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ተአማኒነት ግብረ ሃይል”ተቋቋመ። ===================== አዲስ አበባ 21/06/2016ዓ.ም (የንቀትሚ) ”የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ተአማኒነት ግብረ ሃይል” የሰነድ መዋዕለ ንዋዮችን የአክሲዮን፣ የቦንድ እና ሌሎች ገንዘባዊ ዋጋ ያላቸውን ሰነዶች የግብይት ስርዓት ህጋዊነት ለማረጋገጥና ለመቆጣጠር እንዲቻል ግብረ ሀይሉ የሚጠቅም ነው:: የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር፣ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትህ ሚኒስቴር ፣ የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን፣ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን እንዲሁም በፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት መካከል የትብብርና የቅንጅት የመግባቢያ ስምምነት የተፈረመ ሲሆን የስምምነቱ ዋና አላማ የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያን ህጋዊ እና ከወንጀል ድርጊቶች የፀዳ ለማድረግ በተቋማቱ መካከል ቋሚና ቀልጣፋ ቅንጅታዊ የአሰራር ስርዓት ለመዘርጋት እንዲሁም ውጤታማ የሕግ ስርዓት በመፍጠር የካፒታል ገበያውን ተዓማኒነት ማረጋገጥ ነው፡፡ በዘርፉ ዘላቂ ቅንጅታዊ የአሰራር ስርዓት መዘርጋቱ የካፒታል ገበያ ተአማኒነትን ለመፍጠር፣ ህጋዊ የግብይት ስርዓትን ለማረጋገጥ ፣ ህግ በሚተላለፉ አካላት በህግ እንዲጠየቁ የማድረግ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አለው፡፡

Share this Post