የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር በዋና ዋና ሀገራዊ የማክሮ ኢኮኖሚ ዘርፎች አፈፃፀም ዙሪያ ውይይት አደረገ

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር በዋና ዋና ሀገራዊ የማክሮ ኢኮኖሚ ዘርፎች አፈፃፀም ዙሪያ ውይይት አደረገ ======================= አዲስ አበባ 04/07/2016ዓ.ም (የንቀትሚ) የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አመራሮችና ሰራተኞች በ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት በተመዘገቡ ዋና ዋና ሀገራዊ የማክሮ ኢኮኖሚ ዕቅድ አፈፃፀም ዙሪያ ውይይት አካሂደዋል፡፡ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ ገብረመስቀል ጫላ በሁሉም ዘርፎች ያለን ሀገራዊ የ6 ወር አፈፃፀም ለተቋሙ ሰራተኞች መቅረቡ እንደ ሀገር በኢኮኖሚ፣በማህበራዊ እንዲሁም በአስተዳደር ዘርፎች በምን ደረጃ እንደምንገኝ ሁሉም ሰራተኛ ግንዛቤ እንድኖረው ያግዛል ብለዋል፡፡ የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማው ጥንካሬዎችን አጠናክረን እንድንቀጥል፤የታዩ ድክመቶችን ደግሞ አርመን እንድንሄድ እንደ ተቋምም ያሉትን ክፍተቶች በመለየት እንድንሰራ ሲለሚያግዝ ጠቀሜታው የጎላ መሆኑን ጠቅሰዋል:: ቁርጠኛ አመራር መኖር እንዲሁም የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ ተነድፎ መተግበሩ ለተመዘገበው የተሻለ ውጤት ምክንያት እንደሆነ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የጥራትና መሰረተ ልማት ማረጋገጫ ዘርፍ ሚኒስቴር ዴኤታው አቶ እንዳለው መኮንን ተናግረዋል፡፡ ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ በማዘጋጀትና በመተግበር ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ በመቻሉ በብዙ ችግሮች ውስጥም ሆነን እድገት እየተመዘገበ እንደሚገኝ ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡ የወጪ ንግድ አፈጻጸምም የተሻለ ስኬት እያስመዘገበ መሆኑ ለአብነትም ባለፉት ሰባት ወራት ከአገልግሎት ወጪ ንግድ ብቻ ከ4 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር በላይ መገኘቱን ተነግሯል።

Share this Post