ሁሉንም ተቋማዊ አገልግሎቶች በኦን ላይን ለመስጠት የሚያስችል የሲስተም ማልማት ስራ እየተሰራ ነው፡፡

ሁሉንም ተቋማዊ አገልግሎቶች በኦን ላይን ለመስጠት የሚያስችል የሲስተም ማልማት ስራ እየተሰራ ነው፡፡ ============= አዲስ አበባ 07/07/2016ዓ.ም (ንቀትሚ) ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር በንግድ ፈቃድና ምዝገባ አገልግሎት የጀመረውን የዲጂታል አገልግሎት በማስፋት ሁሉንም ተቋማዊ አገልግሎቶች ዲጂታል ለማድረግ የሲስተም ማልማት ስራ እየሰራ መሆኑን የላይሰንሲንግና ሬጉላቶሪ መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ጅራታ ነመራ ገለጹ፡፡ ሚኒስቴር መ/ቤቱ ከጥር 2013 ዓ.ም ጀምሮ የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎትን በኦን ላይን መስጠት የጀመረ ሲሆን በዘንድሮው በጀት አመት እስከ መጋቢት 4 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ 1,751,555 አገልግሎቶች በኦንላይን መስጠት መቻሉን የገለፁት አቶ ጅራታ በቀጣይ ተቋሙ ደረጃ በደረጃ ሁሉንም የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች በኦንላይን መስጠት የሚያስችል ሲስተም የማልማት ስራ በመጠናቀቅ ላይ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ በቅርቡ የውህደት አገልግሎትና የወጪ ንግድ አገልግሎት የኮንትራት ውል ምዝገባ አገልግሎት በኦንላይን ለመስጠት ዝግጅት የተጠናቀቀ ሲሆን ከሌሎች ተቋማት ጋር እንደ ብሄራዊ መታወቂያ አገልግሎትና ገቢዎች ሚኒስቴር እንዲሁም ብቃት ከሚያረጋግጡ ተቋማት ጋር የሲስተም ማናበብ ስራ እየተሰራ በመሆኑ ተገልጋዮቻችን አገልግሎት ለማግኘት የሚፈለግባቸውን መረጃ ከሲስተም በቀላሉ መጠቀም የሚቻልበትን ሁኔታ ይፈጥራል ሲሉ አቶ ጅራታ ተናግረዋል፡፡

Share this Post