ኢትዮጵያ እያስመዘገበች ላለው ኢኮኖሚያዊ እድገት የንግድ ዘርፉ አዎንታዊ ሚና አበርክቷል

ኢትዮጵያ እያስመዘገበች ላለው ኢኮኖሚያዊ እድገት የንግድ ዘርፉ አዎንታዊ ሚና አበርክቷል ================= አዲስ አበባ 14/07/2016ዓ.ም (ንቀትሚ) ኢትዮጵያ ላስመዘገበቻቻው ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ እድገቶች የንግድ ዘርፉ የበኩሉን አዎንታዊ ሚና አበርክቷል ሲሉ በኢፌዲሪ የህዝብ ተወከዮች ም/ቤት የንግድና ቱሪዝም ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ አይሻ ያህያ ገለጹ፡፡ ኢትዮጵያ እያስመዘገበችው ያለው ኢኮኖሚያዊ እድገት ቀጣይነት እንዲኖረው ዘርፈ ብዙ ስራዎቸ እየተሰሩ ነው ያሉት ሰብሳቢዋ የሀገራችን ንግድ ዘርፍ አሰራሩን በማዘመን የንግዱን ማህበረሰብ እና የሀገርን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ የንግድ ስርዓት ለመገንባት የተሰራው ስራ ጥሩ ውጤት አስመዝግቧል ሲሉም ተናግረዋል፡፡ የዓለም ንግድ ድርጅት ለሀገራችን የተስፋፋ ገበያና ተደራሽነት፣ የታሪፍ ቅናሽ፣ ከውጪ ሀገራት የንግድ ተቋማት ጋር ትስስርን ለማጠናከር እንዲሁም የንግድ አለመግባባትን በህግ ማእቀፍ ለመፍታት ያስችላል ሲሉም ሰብሳቢዋ አመላክተዋል። የአፍሪከ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና የገበያ እድልን በማስፋፋት ንግዱን ማሳለጥ የሚያስችል በመሆኑ የተጀመሩትን ዝግጅቶች አጠናቆ ወደ ተግባር በመግባት ማህበረሰባዊ እና ሀገራዊ ጥቅምን መጎናጸፍ ያስፈልጋልም ሲሉ የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ አሳስበዋል፡፡

Share this Post