የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ፍሰሀ ይታገሱ በድሬደዋ የሚገኝውን የናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካን ጎበኙ።

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ፍሰሀ ይታገሱ በድሬደዋ የሚገኝውን የናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካን ጎበኙ። ================= አዲስ አበባ13/08/2016ዓ.ም (ንቀትሚ) የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴኤታ የድሬደዋን የሲሚንቶ ፋብሪካ እንቅስቃሴ ጎብኝተዋል። በሀገሪቱ የተሻለ የማምረት አቅም ካላቸው የሲሚንቶ ፋብሪካዎች ውስጥ አንዱ የሆነው ናሽናል ሲሚንቶ በአመት 1.3ሚሊየን ኩንታል በማምረት ወደ ገብያ ያቀርባል። አሁን ላይ ፋብሪካው ለማምረቻነት የሚጠቀምበትን ኮል ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት ፍቃድ አለማግኝት እንዲሁም የውጭ ምንዛሪ እጥረት ለስራቸው እንቅፋት እንደሆነባቸው ተገልጿል። እነዚህንና መሰል በዘርፍ ላይ የሚታዩ ችግሮችን ለመቅረፍ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በጋራ እንደሚሰራ ሚኒስትር ዴኤታው ጠቁመዋል::

Share this Post