በአማራ ክልል የንግድ ፍቃድ እድሳት መስጫ ቀናት ተራዘመ

በአማራ ክልል የንግድ ፍቃድ እድሳት መስጫ ቀናት ተራዘመ ======================== አዲስ አበባ 14/8/16 (ንቀትሚ) በአማራ ክልል የንግድ ፍቃድ እድሳት አገልግሎት መስጫ ቀናት በድጋሚ ለሦስት ወራት ተራዝሟል፡፡ በክልሉ በጋጠመው የጸጥታ ችግር ምክንያት የንግድ ፍቃድ እድሳት በተወሰነው የጊዜ ገደብ ውስጥ መከናወን ባለመቻሉ እስከ ሰኔ 30 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ያለቅጣት የንግድ ፍቃድ እድሳት አገልግሎት የሚሰጥበት ጊዜ ተራዝሟል፡፡ በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት ክልሉ ለ357536 ደንበኞች በኦንላይን ንግድ ምዝገባና ፍቃድ አገልግሎት ለመስጠት አቅዶ ለ207181 ደንበኞች አገልግሎት በኦንላይን ተሰጥቷል፡፡

Share this Post