=======================
አዲስ አበባ 06/09/2016ዓ.ም (ንቀትሚ) ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር አቶ ገብረመስቀል ጫላ ንብረትነቱ የህንድ ባለሀብት የሆነው Arti steel ዓለም አቀፍ ኩባንያ የአፍሪካ እና የኢትዮጵያ ተወካዮች ጋር ተወያዩ፡፡
በውይይታቸውም በምርት ማሳያ ቦታ ፖሊሲ እና ኩባንያው በዋጋ እና በጥራት ተወዳዳሪ ሆኖ ውጤታማ መሆን በሚችልባቸው ጉዳዮች ላይ በስፋት መክረዋል፡፡
ዓለም አቀፍ ኩባንያው ያለበትን የግብአት እጥረት ለመቅረፍ ማእድንን ጨምሮ ኢትዮጵያ ባሏት እምቅ የኢንቨስትመንት አማራጮች ላይ ኢንቨስት እንዲያደርግ ሚኒስትሩ ጋብዘዋል፡፡
ከሀገር ውስጥ ኢንቨስትመንት በተጨማሪ በኤክስፖርት ዘርፍ እንዲሰማሩ እንዲሁም የድሬዳዋን ነፃ የንግድ ዞን በመጠቀም የገቢ ንግድን ማሳለጥ እንደሚችሉ አቶ ገብረመስቀል አስረድተዋል፡፡
በቀጣይም Arti steel ዓለም አቀፍ ኩባንያ በሀገራችን የሚያካሂዳቸውን ኢንቨስትመንቶች ማሳለጥ በሚቻልባቸው ሁኔታዎች እና የህንድ እና የኢትዮጵያን የጋራ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ በሚችሉ የንግድና ኢንቨስትመንት ስራዎች ላይ በጋራ ለመስራት ከስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡