የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከተጠሪ ተቋማት፣ ከክልልና የከተማ አስተዳደር የንግድና ገበያ ልማት ቢሮዎች ጋር ለሁለት ቀናት በአዳማ ሲያካሂድ የነበረውን የዘጠኝ ወራት እቅድ አፈጻጸም ግምገማውን አጠናቋል።

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከተጠሪ ተቋማት፣ ከክልልና የከተማ አስተዳደር የንግድና ገበያ ልማት ቢሮዎች ጋር ለሁለት ቀናት በአዳማ ሲያካሂድ የነበረውን የዘጠኝ ወራት እቅድ አፈጻጸም ግምገማውን አጠናቋል። ================= አዲስ አበባ 10/09/2016ዓ.ም (ንቀትሚ) በሀገር አቀፍ ደረጃ በንግድ ዘርፍ የሚካሄደውን የንግድ ሳምንት መርሀ ግብር፣ የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ለንግድ ዘርፍ መዘመን ያለውን አስተዋጽኦ እንዲሁም ለውጭ ባለሀብቶች የተከፈቱ የንግድ መስኮች በተመለከተ ሰነዶች ቀርበው በዛሬው እለት ውይይት ተደርጎባቸዋል። በውይይቱ የንግድ ሳምንቱ እንደ ሀገር በኢኮኖሚ ዘርፍ ላይ ያለንን አቅም ለማሳደግ የሚጠቅም በመሆኑ በዘርፍ ላይ ዲጂታላይዜሽንን በመተግበር በቅንጅት እየተሰሩ ያሉ ስራዎች የሚበረታቱ በመሆናቸው ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ ተጠቁሟል።

Share this Post