በሀገር ውስጥ ንግድ ላይ የሚያተኩር የፓናል ውይይት በመካሄድ ላይ ነው፡፡

በሀገር ውስጥ ንግድ ላይ የሚያተኩር የፓናል ውይይት በመካሄድ ላይ ነው፡፡ ============== አዲስ አበባ ነሐሴ 20 ቀን 2016 ዓ.ም(ንቀትሚ) የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ያዘጋጀው “የኢትዮጵያን ይግዙ” የንግድ ሳምንት አካል የሆነውና ትኩረቱን በሀገር ውስጥ ንግድ ላይ የሚያደርግ የፓናል ውይይት ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ በፓናል ውይይቱ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ(ዶ/ር) ባደረጉት ንግግር የንግድ መግቢያ በር ከሆነው የንግድ ፍቃድ አሰጣጥ እስከ ቁጥጥር ሂደቱ ድረስ ሰፊ ውይይት በባለሙያወችና ባለድርሻ አካላት እንደሚካሄድ ገልፀዋል፡፡ ሚኒስትሩ በንግግራቸው የንግድ ስርዓትና ላይሰንሲንግን ለማዘመን በተደረገው ስራ 89 በመቶ የሀገራችን ነጋዴዎች በኦንላይን አገልግሎት ባሉበት ሆነው ንግድ ፍቃዳቸውን ማውጣትና መደስ እንደቻሉ ተናግረዋል፡፡ ሸማቹ ህብረተሰብ በዋጋ ንረትና በአቅርቦት እጥረት እንዳይቸገር1066የቅዳሜና እሁድ ገበያዎች መቋቋመቸውን የተናገሩት ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ካለን የህዝብ ቅጥር አኳያ በቂ ባለመሆናቸው ማሳግ ላይ እንደሚሰራ አብራርተዋል፡፡ በተዘረጋው የታለመለት የነዳጅ ድጎማ ስርዓት መንግስት የነበረበትን 179 ቢሊዮን ብር እዳ ወደ 70 ቢሊዮን ብር ማውረድ መቻሉና ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ገልፀዋል፡፡

Share this Post