የእሁድ ገበያዎች የበዓል ገበያው የአቅርቦት እጥት እንዳያጋጥም ሸማቹንና አምራቹን በቀጥታ በማገናኘት ገበያን የማረጋጋት ሚናቸውን እየተወጡ ነው ፡፡

የእሁድ ገበያዎች የበዓል ገበያው የአቅርቦት እጥት እንዳያጋጥም ሸማቹንና አምራቹን በቀጥታ በማገናኘት ገበያን የማረጋጋት ሚናቸውን እየተወጡ ነው ፡፡ ============ አዲስ አበባ ነሀሴ 27 /2016 ዓ.ም (ንቀትሚ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ የእሁድ ገበያዎች የበዓል ገበያው የአቅርቦት እጥት እንዳያጋጥም ሸማቹንና አምራቹን በቀጥታ በማገናኘት ገበያን የማረጋጋት ሚናቸውን እየተወጡ መሆኑን አስታወቀ፡፡ በክልሉ የተቋቋሙ የሰንበት ገበያዎች አምራቾች የምግብ ምርታቸውን ያለደላላ ጣልቃገብነት ለገበያው በማቅረብ ህብረተሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ የሚሸምትበትና ለአምራቹም የገበያ ትስስር የሚፈጠርበት እንዲሁም ሸማቹን ከሰውሰራሽ የዋጋ ንረት ለመከላከልና የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት ከፍተኛ ሚና እየተወጡ መሆኑን የክልሉ ገበያ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ በፌስ ቡክ ገፁ አስታውቋል፡፡

Share this Post