የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ(ዶ/ር) ከብሔራዊ ስትሪንግ ኮሚቴ ጋር ተወያዩ፡፡
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ(ዶ/ር) ከብሔራዊ ስትሪንግ ኮሚቴ ጋር ተወያዩ፡፡ =========================== አዲስ አበባ ነሐሴ 30/2016ዓ.ም (ንቀትሚ) የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) በአለም ንግድ ድርጅት፣ በቀጠናዊ እና የሁለትዮሽ ድርድሮች ዙሪያ ከብሔራዊ ስትሪንግ ኮሚቴ አባላት ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡ ሚኒስትሩ ከብሔራዊ ስትሪንግ ኮሚቴ ጋር በዓለም ንግድ ድርድር እና የሁለትዮሽ ድርድሮች ዙሪያ የተወያዩ ሲሆን የአለም ንግድ ድርጅት የአባልነት ጥያቄ ዙሪያ እየተካሄደ ባለው ዝግጅት ላይ ሰፊ ውይይት አካሂደዋል፡፡ በውይይቱ ለአምስተኛው የስራ ቡድን ውይይት እየተደረጉ ባሉ ዝግጅቶችና ቀሪ ስራዎች ላይ ትኩረት የተደረገ ሲሆን በመጪው ጥቅምት ለሚካሄደው አምስተኛው የስራ ላይ ቡድን ውይይት የሚቀርቡ ሰነዶችና መረጃዎች በስፋት ተገምግመዋል፡፡ ከብሔራዊ ኮሚቴው ጋር በተደረገው ውይይት ኢትዮጵያ የአለም ንግድ ድርጅት አባል ለመሆን እስከ ዛሬ የሄደችበት ጉዞ የተነሳ ሲሆን ለአለም ንግድ ድርጅት አባልነት ለሚደረገው ድርድር በሀገራችን እየተደረጉ የሚገኙ የኢኮኖሚ ሪፎርሞችና የፖሊሲ ማሻሻያዎች ድርጅቱን ለመቀላቀል ለሚደረገው ጥረት አጋዥ እንደሚሆኑ ሚኒስትሩ ተናግረዋል ፡፡