የሀገራችንን የኤክስፖርት ምርቶች በማስተዋወቅ እና የገበያ ትስስርን በሚያጠናክሩ ጉዳዮች ዙርያ ውይይት ተካሄደ፡፡
=================
አዲስ አበባ 07/01/2017 ዓ.ም (ንቀትሚ) በኢትዮጵያ የጀርመን ኤምባሲ የኢኮኖሚ ጉዳዮች ሃላፊ ሚስ ሩቤካ ኢለት እና በኢትዮጵያ የጀርመን ኤምባሲ የግብርና ጉዳዮች ሃላፊ ሚስተር አሌክስ ዋልተር በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የወጪ ንግድ ፕሮሞሽን መሪ ስራ አስፈፃሚ ከሆኑት አቶ ሊቁ በነበሩ ጋር ተወያይተዋል፡፡
ውይይቱ በዋነኝነት ኢትዮጵያ ለወጪ ንግድ የምታቀርባቸውን ምርቶች በማስተዋወቅ እና በሁለቱ ሀገራት የገበያ ትስስሮችን ማጠናከር ላይ ያተኮረ ሲሆን በተጨማሪም ኢትዮጵያ ለወጪ ንግድ የምታቀርባቸው ምርቶች በጀርመን እና በአውሮፓ ገበያዎች በተሻለ ለማስተዋወቅ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ በትብብር ለመስራት የሚያስችል ሃሳብ ተለዋውጠዋል፡፡
የኤምባሲው የስራ ሃላፊዎች በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የሚገኘውን የወጪ ምርቶች ማሳያ ማዕከል የጎበኙ ሲሆን ኢትዮጵያ ለወጪ ገበያ የምታቀርባቸውን ምርቶች እና አገልግሎቶች በአንድ ቦታ ለዕይታ መቅረባቸው የሀገራችን የኤክስፖርት ምርቶች በማስተዋወቅ ረገድ ከፍተኛ ሚና እንዳለው ተናግረዋል፡፡