የንግድ ትስስርና የወጪ ንግድ ፕሮሞሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ከኮሜሳ ሴቶች ቢዝነስ ፌደሬሽን አባላት ጋር ተወያዩ፡፡

የንግድ ትስስርና የወጪ ንግድ ፕሮሞሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ከኮሜሳ ሴቶች ቢዝነስ ፌደሬሽን አባላት ጋር ተወያዩ፡፡ ============= አዲስ አበባ፡ መስከረም 20/2017 ዓ.ም (ንቀትሚ) በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የንግድ ትስስርና የወጪ ንግድ ፕሮሞሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ያስሚን ወሀብረቢ በኮሜሳ የሴቶች ቢዝነስ ፌደሬሽን አባላትን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡ ሚኒስትር ዴኤታዋ በደቡብና ምስራቅ አፍሪካ ሀገራት የጋራ ገበያ (ኮሜሳ) የሴቶች ቢዝነሽ ፈደሬሽን ልዑክን ጋር ፌዴሬሽኑ በ2025 ግንቦት ወር በኢትዮጵያ ለሚያካሂደው ጉባኤ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በኩል ሊደረግለት የሚችለውን ድጋፍ አስመልክቶ ውይይት አድርገዋል፡፡ በኮሜሳ ችፍ ኤክስኪዩቲቨ ኦፊሰር ሚስተር ችካኩላ ሚቲ በኢትዮጵያ በኩል ለገበያ ማህበሩ ጉባኤ መሳካት ሊደረጉ የሚገባቸውን ነጥቦች አንስተዋል፡፡ የንግደና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የንግድ ትስስርና የወጪ ንግድ ፕሮሞሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ያስሚን ወሀብረቢ በበመኩላቸው ኢትዮጵያ የተለያዩ ጉባኤዎችን በማስተናገድ የተሻለ ልምድ እንዳላት ጠቅሰው የገበያ ማህበሩ ጉባኤውን በአዲስ አበባ ለማካሄድ መወሰኑ ትክክለኛ ሀገርና ከተማ እንደመረጠ ተናግረዋል፡፡ የኢትያጵያ መንግሰት የተለያዩ የኢኮኖሚ ሪፎርሞችን እያከናወነ እንደሚገኝ በመጠቆም በኮሜሳ የሴቶች ቢዝነስ ፌደሬሽን ለሚያካሂደው ጉባኤ መሳካትም ሚኒስቴር መስሪ ቤቱ እና መንግስት ድጋፍ እንደሚያደርግ ያላቸውን እምነት ተናግረዋል፡፡ በመጨረሻም በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የተገነባውን የወጪ ንግድ ምርቶች ማሳያ ማዕከል በእንግዶቹ ተጎብኝቷል፡፡

Share this Post