የንግድ ትስስር እና ወጪ ንግድ ፕሮሞሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ያስሚን ወሀብረቢ የቻይና ባለሀብቶችን በቢሯቸው ተቀብለው አነጋገሩ

የንግድ ትስስር እና ወጪ ንግድ ፕሮሞሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ያስሚን ወሀብረቢ የቻይና ባለሀብቶችን በቢሯቸው ተቀብለው አነጋገሩ ===================================== አዲስ አበባ 28/2/2017(ንቀትሚ) በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የንግድ ትስስር እና ወጪ ንግድ ፕሮሞሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ያስሚን ወሀብረቢ የቻይና ባለሀብቶችን ተቀብለው በንግድ እና ኢንቨስትመንት ጉዳዮች ዙሪያ አወያይተዋል። በውይይታቸውም ኢትዮጵያ በወጪ ንግድ ያላትን ምቹ ሁኔታ እና መልካም እድል የገለጹላቸው ሲሆን በኢትዮጵያ ውስጥ ኢንቨስት አድርገው ኤክስፖርት ማድረግ እንዲችሉ እና የሁለቱ ሀገራት የንግድ ግንኙነት ይበልጥ የሚሻሻልበትን ሁኔታ ለመፍጠር ሚኒስቴር መ/ቤቱ አስፈላጊውን ሁኔታ እንደሚያመቻች ገልጸውላቸዋል፡፡ ባለሀብቶቹ በበኩላቸው ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ምርጥ የኢንቨስትመንት መዳረሻቸው መሆኗን ገልጸው በተለይም በወጪ ንግድ ዘርፍ ኢንቨስትመንት ላይ ለመሳተፍ ሙሉ ፍላጎት አንዳላቸው ገልጸዋል፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ በርካታ የቻይና ካምፓኒዎች ውጤታማ ሆነው እየሰሩ መሆኑን ጠቅሳው በቀጣይ በርካታ የቻይና ባለሀብቶችን ወደ ኢትዮጵያ በመሳብ በጥራጥሬ፣ በቅባት እህሎች፣ በቁም እንሰሳት፣በጫት እና ሌሎችም ኤክስፖርት ተኮር ምርቶች ላይ በትብብር ለመስራት ያላቸውን ፍላጎት አሳይተዋል፡፡ በመጨረሻም በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የሚገኘውን ቋሚ የኢትዮጵያ ወጪ ንግድ ማሳያ ማእከልን ጎብኝተዋል፡፡

Share this Post