የዓለም ንግድ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ንጎዚ ኦኮንጆ በቢሮዬ ተቀብዬ ተወያይተናል፡

የዓለም ንግድ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ንጎዚ ኦኮንጆ በቢሮዬ ተቀብዬ ተወያይተናል፡፡ ሀገራችን በዓለም ንግድ ድርጅት እ.ኤ.አ እስከ ከ2003 ዓ.ም ጀምሮ በታዛቢነት ቆይታ ድርድሯን ጀምራለች፡፡ እስካሁን ባለው የድርድር ሂደት አራት ዙር የስራ ቡድን ድርድሮችን ያካሄደች ሲሆን በአጠቃላይ ከአባል ሃገራት ከ900 በላይ ጥያቄ ተነስተው ምላሽ ተሰጥቷል፡፡ የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት ኢትዮጵያ እያካሄደች ያለውን የሃገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም አጀንዳዎች አጋዥ እንደሚሆን በማመን ድርድሩ በአዲስ መልክ እንዲጀመር ተረድጓል፡፡ ኢትዮጵያ ድርድሯን በቀጣይ በሚካሄደው የዓለም የንግድ ድርጅት 14ኛው የሚኒስትሮች ም/ቤት ለማጠናቀቅ እቅዳ እይሰራች የምትገኝ ሲሆን መጋቢት 11 ቀን 2017 ለሚሃኬደው 5ኛው የስራ ቡድን ድርድር ዝግጅት ተጠናቋል፡:፡ በዛሬው ውይይታችንም የድርድር ሂደቱን ለማፋጠን የሚያግዙ ድጋፎች ላይ ከድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ጋር ተወያይተናል፡፡

Share this Post