የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ባለፋት ዘጠኝ ወራት ለ19 ሺህ 834 የምርትና አገልግሎቶች የጥራት ማረጋገጫ አገልግሎት ሰጥቷል፡

የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ባለፋት ዘጠኝ ወራት ለ19 ሺህ 834 የምርትና አገልግሎቶች የጥራት ማረጋገጫ አገልግሎት ሰጥቷል፡፡ ======================= አዲስ አበባ 28/07/2016ዓ.ም(ንቀትሚ) የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት በ2016 በጀት ዓመት በዘጠኝ ወራት ለ19 ሺህ 834 የምርትና አገልግሎቶች የጥራት ማረጋገጫ አገልግሎት በምርት ጥራት የፍተሻ ላብራቶር፣በወጪና ገቢ ምርት ኢንስፔክሽንና የሰርቲፊኬሽን አገልግሎት መስጠቱን አስታዉቋል። በተጨማሪም ተቋሙ በጅቡቲ ወደብ በኩል ለ898,612 ሜ/ቶን የአፈር ማዳበርያ እና የተለያዩ የጅምላ ጭነት እንዲሁም 31,615,978 ሊትር የምግብ ዘይት ኢንስፔክሽን አገልግሎቶች በመስጠት ጥራት ያለው ምርትና አገልግሎት እንዲኖር በማድረግ የሽማቾችን ጤና እና የአካባቢ ደህንነትን የመጠበቅ እንዱሁም ሁሉን አቀፍ አገራዊ እድገት ለማረጋገጥ የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ ይገኛል፡፡ ኢተምድ ዋና መ/ቤቱን በአዲስ አበባ በማድረግ በ9 የተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች ቅርንጫፎችን እንዲሁም በውጭ ሀገር በጅቡቲ ወደብ በመክፈት የጥራት ማረጋገጥ ስራዎችን በማከናወን በማደግ ላይ ያለውን ኢኮኖሚ በአስተማማኝ መሠረት ላይ በመገንባትና ቀጣይነቱን በማረጋገጥ አገራዊ የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ሽግግር ለማምጣት በሚደረገው ርብርብ ውስጥ በመሳተፍ ሀላፊነቱን በመወጣት ላይ የሚገኝ ድርጅት መሆኑን የበጀት ዓመቱ የዘጠኝ ወር እቅድ አፈፃፀም በተገመገመበት መድረክ ላይ ተገልፆል፡፡

Share this Post