በነዳጅ ላይ በተከናወነ የሪፎርም ስራ በነዳጅ ማረጋጊያ ፈንድ ላይ የነበረው 197 ቢሊዮን ብር ዕዳ ወደ 89 ቢሊዮን ብር ማውረድ ተችሏል፡፡

በነዳጅ ላይ በተከናወነ የሪፎርም ስራ በነዳጅ ማረጋጊያ ፈንድ ላይ የነበረው 197 ቢሊዮን ብር ዕዳ ወደ 89 ቢሊዮን ብር ማውረድ ተችሏል፡፡ ================= አዲስ አበባ 9/9/16(ንቀትሚ) የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ዙሪያ ከከተማ አስተዳደርና ከክልል ንግድ ቢሮዎች ከተጠሪ ተቋማት እንዲሁም ከባለድርሻ አካላት ጋር በተደረገው ግምገማ በጥንካሬ ከተከናወኑ ስራዎች አንዱ የነዳጅ ሪፎርም መሆኑን ገልጿል፡፡ ዝቅተኛ ገቢ ያለቸውን ህብረተሰብ ለመደጎም የነዳጅ ሪፎርማ ከሀምሌ 1/2014 ጀምሮ ተግባራዊ የተደረገ ሲሆን ከሐምሌ 1/2015 ዓ.ም ጀምሮ ለህዝብ አገልግሎት የሚሰጡ የከተማ አውቶቢስና አገር አቋራጭ ውጭ ያሉ ከአንድ ሚሊዮን የማያንሱ ተሽከርካሪዎችን ከጥቅል ድጎማ እንዲወጡ በነዳጅ ላይ በተሰራ ጠንካራ ስራ በነዳጅ ማረጋጊያ ፈንድ ላይ የነበረውን 197 ቢሊዮን ዕዳን ወደ89 ቢሊዮን ብር ማውራድ መቻሉን ሚኒስቴር መስሪያቤቱ ገልጿል፡፡ በለፉት ዘጠኝ ወራት ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን የህብረተሰብ ክፍል ለመደጎም 29.2 ቢሊዮን ብር ድጎማ የተደረገ መሆኑን የገለጸው መስሪያቤቱ ከ1580 የነዳጅ ማዳያዎች 1535 በቴሌ ብር የተመዘገቡ ሲሆኑ1453 ትራንዛክሽን የጀመሩ መሆናቸው ተጠቁሟል።

Share this Post