የጥራት መሠረተ ልማት ማረጋገጫ ዘርፋ አመራሮች የተጠሪ ተቋማትን የ2016 በጀት አመት የስድስት ወራት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ግምገማ አከናውነዋል፡፡

የጥራት መሠረተ ልማት ማረጋገጫ ዘርፋ አመራሮች የተጠሪ ተቋማትን የ2016 በጀት አመት የስድስት ወራት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ግምገማ አከናውነዋል፡፡ =================== አዲስ አበባ 07/05/2016ዓ.ም (ንቀትሚ) በግምገማው የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዮት፣ የኢትዮጵያ ስነልክ ኢንስቲትዮት፣ የኢትዮጵያ ተስማሚነት ምዘና ድርጅት እንዲሁም የኢትዮጵያ አክሬዴሽን አገልግሎትን የ2016 በጀት አመት የስድስት ወራት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት በዝርዝር ቀርቦ ውይይት ተከናውናል፡፡ በውይይቱ የጥራት መሠረተ ልማት ማረጋገጫ ዘርፋ ሚኒስቴር ዴኤታ አቶ እንዳለው መኮንን በጥራት ዘርፉ ባለፉት ስድስት ወራት ጥሩ ስራዎች የተሠሩበትና በዘርፉ የላቀ አፈፃፀም የተገኘበት ወቅት መሆኑን ገልፀው አፈፃፀሙ የተሻለ መስራት እንደሚቻል አመላካች መሆኑንም ተናግረዋል፡፡ ሚኒስቴር ዴኤታው አያይዘውም ዝቅተኛ አፈፃፀም ያላቸው ዘርፎች ላይ በቀጣይ ወራት የዕቅድ ክለሳና የድርጊት መርሃ ግብር በመቅረፅ በትኩረት መስራት እንደሚገባ አሳስበው በቀጣይ ወራት ጥሩ ደረጃ ያሉትን የጥራት መሠረተ ልማት ተቋማትን እንዲሁም የሚሠጡትን አገልግሎት ማስተዋወቅ፣ የገበያ አማራጮችን ማስፋት ፣ የፋይናንስ አማራጮችን ማስፋት እና ዘርፉ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት መስራት እንደሚገባ ገልፀዋል።

Share this Post