አዲሱ የንግድ ህግ ለ25 ዓመት እንዲያገለግል ሆኖ የተዘጋጀ ነው፡፡

አዲሱ የንግድ ህግ ለ25 ዓመት እንዲያገለግል ሆኖ የተዘጋጀ ነው፡፡ ================= አዲስ አበባ 22/04/2016ዓ.ም (ንቀትሚ) በ1952 ዓ.ም የወጣው የኢትዮጵያ የንግድ ህግ ለ60 ዓመታት ካገለገለ በኋላ ነበር አዲሱ የንግድ ህግ አዋጅ ቁጥር 1243/2013 የተተካው፡፡ ለዚህም ደግሞ የኢንቨስትመንት ፍሰት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣት፣አካባቢያዊና አለም አቀፋዊ የንግድ ትስስር እየጎለበተ መምጣትና የቴክኖሎጂ እድገት ለአዲሱ የንግድ ህግ መውጣት ዋና መነሻ ምክንያቶች ከሆኑት ውስጥ እደሚጠቀሱ በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የህግ አገልግሎት ስራ አስፈፃሚ አቶ ይርሳው ዘውዴ ይናገራሉ፡፡ አቶ ይርሳው እደሚሉት ቀደም ሲል የነበረው የ1952ዓ.ም የንግድ ህግ በዘመኑ ጊዜውን የቀደመ ቢሆን አሁን ላይ ካለው ነበራዊ ሁኔታ ጋር ደግሞ መሻሻችን የሚፈልግ መሆኑን ያስረዳሉ፡፡ አዲሱ የንግድ ህግ አለም አቀፋዊ ሁኔታው ተለዋዋጭ መሆኑን ግምት ውስጥ ያስገባና የሚፈጠሩ ለውጦችን ተከትሎ እንደ አስፈላጊነቱ ማሻሻያዎች እየተደረገበት ቢያንስ ከ 25 እስከ 50 ዓመት ድረስ እንዲያገለግል ታስቦ ጊዜ ተወስዶና በጥናት ላይ ተመስርቶ የወጣ ህግ መሆኑን አቶ ይርሳው ጠቁመዋል፡፡

Share this Post