ባለፉት 6 ወራት በሀገር አቀፍ ደረጃ ከ 1.5 ሚሊዮን በላይ የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎቶች ተሠጥተዋል፡፡

ባለፉት 6 ወራት በሀገር አቀፍ ደረጃ ከ 1.5 ሚሊዮን በላይ የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎቶች ተሠጥተዋል፡፡ ===================== አዲስ አበባ 18/05/2016ዓ.ም (ንቀትሚ) ባለፉት ስድስት ወራት በሀገር አቀፍ ደረጃ 1ሚሊዮን 545 ሺህ 514 የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎቶች(በኦን ላይን እና በባክ ኦፊስ) መሰጠታቸውን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል። ይህም ከግማሽ አመት እቅድ አንፃር 73.6%አፈፃፀም አለው። የተሠጡት አገልግሎቶች አዲስ የንግድ ምዝገባ፣ አዲስ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ፈቃድ እድሳት፣ ማሻሻያ፣ የንግድ ስም እንዲሁም መሠል 19 የተለያዩ አገልግሎቶችን ያካተተ ነው፡፡ በፌደራል ደረጃ ባለፉት ስድስት ወራት ከ93 ሺህ በላይ የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎቶች በኦን ላይን የተሠጡ ሲሆን በእድሳት ወቅት ቅዳሜና እሁድን ጨምሮ በእረፍት ቀናት አገልግሎት መሠጠቱ ለዘርፉ የተሻለ አፈፃፀም መገኘት ምክንያት ነው፡፡ በ2016 በበጀት አመት በሀገር አቀፍ ደረጃ 2.8 ሚሊዮን የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎቶች አገልግሎቶችን ለመስጠት ታቅዳል፡፡

Share this Post