ከደረጃ በታች የሆኑ ከ 630 ሜትሪክ ቶን በላይ ገቢ ምርቶች ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ ታገደ ፡፡

C በበጀት ዓመቱ ስድስት ወራት የጥራት ቁጥጥር ከተደረገባቸው አስገዳጅ ደረጃ የወጣላቸው ምርቶች መካከል አጠቃላይ መጠኑ 630.21 ቶን የሆነ የተለያዩ የምግብ ውጤቶች፣ የኮንስትራክሽን ዕቃዎች(የአርማታ ብረት፣ቆርቆሮ)፣ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች(የኤልክተሪክ ኬብል፣ኤል ኢ ዲ አምፑል፣ የአሌክትሪክ ሶኬት ማከፋፈያ) የኬሚካል ውጤቶች(የዱቄት ሳሙና) በተደረገ የላብራቶሪ ፍተሻ እና የኢንስፔክሽን ስራ ከደረጃው በታች መሆናቸው በመረጋገጡ ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ ታግደዋል፡፡ በዚህም ሸማቹን ህብረተሰብ ጥራታቸውና ደህንነታቸው ካልተረጋገጠ ምርቶች ለመጠበቅ ከመቻሉም ባሻገር በሀገር ኢኮኖሚ ላይ ሊደርስ የሚችለውን ኪሳራ ለማስቀረት መቻሉን የገለጸው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በቀጣይም የጥራት ማረጋገጥ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስታውቋል፡፡

Share this Post