ከቁም እንስሳት ወጪ ንግድ ከ9 ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ ተገኝ::

ከቁም እንስሳት ወጪ ንግድ ከ9 ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ ተገኝ:: ====================== አዲስ አበባ 13/05/ 2016 (ንቀትሚ) በ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያዎቹ ስድስት ወራት 130 ሺህ 237 የቁም እንስሳትን ወደ ውጪ ገበያ በመላክ 9 ነጥብ 276 ሚሊየን ዶላር ገቢ መገኘቱን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ በበጀት ዓመቱ ስድስት ወራት ወደ የመን፣ ኦማን፣ ጂቡቲ፣ ሶማሊያ፣ ሊቢያ እና ሳዑዲ ዓረቢያ መዳረሻ አገራት 127 ሺህ 464 በጎች፣ 2 ሺህ 299 ግመሎች እና 474 የዳልጋ ከብቶችን በመላክ 9 ነጥብ 276 ሚሊየን ዶላር ገቢ መገኘቱን ያስታወቀው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ይህም የእቅዱን 81.2 በመቶ ማሳካት ተችሏል፡፡ ከዘርፉ የተገኘው አፈጻጸም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በእንስሣት የ106 ሺህ እንዲሁም በገቢ የ1 ነጥብ 51 ሚሊየን ዶላር ብልጫ አሳይቷል።

Share this Post