13ኛው የዓለም ንግድ ድርጅት የሚኒስትሮች ጉባኤ በተባበሩት አረብ ኤመሬቶች /በአቡዳቢ/ በመካሄድ ላይ ይገኛል::

13ኛው የዓለም ንግድ ድርጅት የሚኒስትሮች ጉባኤ በተባበሩት አረብ ኤመሬቶች /በአቡዳቢ/ በመካሄድ ላይ ይገኛል:: =================== አዲስ አበባ 18/06/2016ዓ.ም (ንቀትሚ) ኢትዮጵያ ከፌብሩዋሪ 26-29 በሚካሄደው የዓለም ንግድ ድርጅት 13ኛው የሚኒስትሮች ጉባኤ በተባበሩት አረብ ኤመሬቶች በአቡዳቢ እየተሳተፈች ትገኛለች። የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትርና የዓለም ንግድ ድርጅት እና ቀጣናዊ ንግድ ትስስር ጉዳዮች ዋና ተደራዳሪ አቶ ገብረመስቀል ጫላ የተመራ የልዑካን ቡድን ተሳትፎ እያደረገ ሲሆን አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ እና የዓለም አቀፍና ቀጣናዊ ንግድ ትስስር ጉዳዮች ምክትል ዋና ተደራዳሪ፣ ዶ/ር እዮብ ተካልኝ የገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታና የብሔራዊ እስትሪንግ ኮሚቴ አባል እንዲሁም አምባሳደር ኡመር ሑሴን የተባበሩት አረብ ኤመሬቶች የኢትየጵያ አምባሳደር እና የተለያዩ ተቋማት ተወካዮች ኢትዮጵያን በመወከል ተሳትፈዋል፡፡

Share this Post