የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ ገብረመስቀል ጫላ ከአለም ባንክ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ።

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ ገብረመስቀል ጫላ ከአለም ባንክ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ። ====================== አዲስ አበባ 06/05/2016ዓ.ም (ንቀትሚ) የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ ገብረመስቀል ጫላ ከአለም ባንክ የኢትዮጵያ፣የሳውዝ ሱዳን፣ሱዳን፣ኤርትራ፣ሀገራት ዳይሬክተር አቶ ኡስማን ዲኦኔ ጋር በብሔራዊ የጥራት መሰረተ ልማት የምዕራፍ አንድ አፈጻጸም ዙርያ ውይይት አካሂደዋል። በውይይቱ የንግድ ስርዓትን በማዘመን እና ቴክኖሎጂን በመጠቀም በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ሆኖ ለመገኝት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙርያ ውይይት የተካሄደ ሲሆን ለዋና ዳይሬክሩ በብሔራዊ የጥራት መሰረተ ልማት (NQI) ዋና ዋና ተግባራት ዙርያ ማብራርያ ተደርጎላቸዋል፡፡ እንደ ኢትዮጵያ ላሉ በማደግ ላይ ለሚገኙ ሀገራት በአለማቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ለመሆን ጥራት ወሳኝ በመሆኑ በዚህም ትልቁን ሚና የሚይዘው የግሉ ዘርፍ ወደ ውጪ ለሚያወጣቸው ምርቶች አለማቀፍ የጥራት ደረጃቸውን አሟልተው እንዲወጡ ለማስቻል በብሄራዊ የጥራት ደረጃ መሰረተ ልማት ላይ የሚሰሩ ስራዎች ትልቁን ቦታ እደሚይዙ በማብራያው ተገልጿል፡፡ በጥራት መሰረተ ልማት ዙርያ ሀገሪቱ አለማቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የላብራቶሪ ፍተሻን ተግባራዊ ከማድረግ ጀምሮ በርካታ ምርቶች የጥራት ደረጃቸውን አሟልተው እንዲወጡ በማስቻል ረገድ ከአለም ባንክ የሚደረገውን ድጋፍ በመጠቀም የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር እንደ ሀገር እያከናወነ የሚገኝውን ስራን ተዘዋውረው የተመለከቱን ዋና ዳይሬክተሩ የሀገሪቱ መንግስት ለጥራት መሰረተ ልማት የሰጠውን ትኩረት አበረታች በመሆኑ በቴክኖሎጂ በሰው ሀይል እና መሰል ድጋፎችን ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

Share this Post