ብሔራዊ የኢ-ኮሜርስ ስትራቴጂ በመንግስት ልዩ ትኩረት በመስጠት የማያስፈጽመው ነው:- የኢፌድሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ

ብሔራዊ የኢ-ኮሜርስ ስትራቴጂ በመንግስት ልዩ ትኩረት በመስጠት የማያስፈጽመው ነው:- የኢፌድሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ =================== አዲስ አበባ 21/08/2016(ንቀትሚ) የኢፌድሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ብሄራዊ የኢ-ኮሜርስ ስትራቴጂ መንግስት በልዩ ትኩረት የሚያስፈጽመው ነው ሲሉ ገለጹ። በመንግስት ልዩ ትኩረት ከተሰጣቸው ዘርፎች መካከል አንዱ ብሔራዊ የኢ-ኮሜርስ ስትራቴጂ መሆኑን የገለጹት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የዲጂታል ቴክኖሎጂ እድሎችን በመጠቀም የስራ እድል መፍጠር እና የውጭ ምንዛሪ ግኝታችንን በማሳደግ ሁሉ አቀፍ እና ቀጣይነት ያለው ሁለተናዊ ልማትን ለማሳለጥ ያስችላል ብለዋል። የኢ-ኮሜርስ ስትራቴጂ ዝግጅትና ትግበራ ሃገራዊ የልማት ፕሮግራሞቻችንን በስኬት ለመፈጸም፣ ኢኮኖሚያችንን በቀጣይነት ለማሳደግ እና በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪነታችንን ለማሻሻል የቴክኖሎጂ እና የኢ-ኮሜርስ ሀይልን ለመጠቀም ምቹ ሁኔታዎችን እንደሚፈጥር ይጠቃል ሲሉም የኢፌድሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ገልፀዋል።

Share this Post