የኢትዮ-ብራዚል የቢዝነስ ፎረም በሳኦ ፓሎ እየተካሄደ ይገኛል።

የኢትዮ-ብራዚል የቢዝነስ ፎረም በሳኦ ፓሎ እየተካሄደ ይገኛል። አዲስ አበባ 05/09/2016 (ንቀትሚ) የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ፣በኢትዮጵያ የብራዚል ኤምባሲ ከዋፋ ማርኬቲንግና ፕሮሞሽን እንዲሁም ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር ያዘጋጀውን የኢትዮ-ብራዚል የንግድና የኢንቨስትመንት ፎረም በሳኦ ፖውሎ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል። በፎረሙ ከኢትየጵያና ብራዚል የተውጣጡ ከ250 በላይ ባለሃብቶችና ኩባንያዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ። ፎረሙ ለብራዚል ባለሃብቶችና ኩባንያዎች ኢትዮጵያን ዋነኛ የኢንቨስትመንት መዳረሻ እንድትሆን በማድረግ ረገድ ከፍ ያለ ፋይዳ እንደሚኖረው የሚጠበቅ ሲሆን በተለይም በግብርናና አግሮፕሮሰሲንግ፣ በኢንዱስትሪ፣ በማዕድን፣ በጨርቃ ጨርቅና በሌሎች የኢንቨስትመንት ዘርፎች ያለውን ሰፊ ዕድል መጠቀም ያስችላል ተብሏል። በተጨማሪም ፎረሙ ኢትዮጵያውያን ባለሃብቶችን ከብራዚል አቻዎቻቸው ጋር በመጣመር እንዲሰሩ ለማስቻልና የኢትዮጵያን ምርቶች በብራዚል ገበያ በስፋት ተደራሽ ለማድረግ አይነተኛ ሚና እንደሚኖረው በመድረኩ ላይ ተገልጿል። በፎረሙ ላይ በብራዚል የኢትዮጵያ አምባሳደር ጣፋ ቱሉ፣ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ፍስሐ ይታገሱ፣ የብራዚል የንግድ የኢንዱስትሪና አገልግሎት ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ኃላፊ ማርሲዮ ኤልያስ ሮዛ እንዲሁም የሳኦ ፖውሎ ከተማ የዲፕሎማሲ ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ምክትል ኃላፊ ሳሞ ቶሳቲና ሌሎች የሁለቱ አገራት የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ ባለሃብቶችና የድርጅት አስተዳዳሪዎች መሳተፋቸው ተገልጿል። በመድረኩ የሳኦፖሎ ንግድ ም/ቤት ከሀገራችን የንግድ ም/ቤት ጋር የሁለትዮሽ ንግድ ስምምነት እንደሚፈራረሙ ይጠበቃል። በተጨማሪም የሁለቱ ሀገራት የንግድ ልኡኮች የንግድ ዘርፋን የሚያጠናክር ውይይቶችን እንደሚያደርጉ በመድረኩ ተገልጿል።

Share this Post