በዘጠኝ ወሩ የዕቅድ አፈጻጸም ላይ ውይይት ተካሄደ።
========================
አዲስ አበባ 30/08/2016 ዓ.ም(ንቀትሚ) የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አመራሮችና ሠራተኞች በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት በተቋሙ ታቅደው በተከናወኑ ተግባራት ፣ጠንካራ ጎኖች ፣ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ላይ ውይይት አካሂደዋል፡፡
በውይይቱ ላይ የተገኙት የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ ገ/መስቀል ጫላ ዕቅድ አፈጻጻሙ በየደረጃ ያለው የተቋሙ ሠራተኞች ውጤት በመሆኑ በአፈጻጸም ወቅት የተከናወኑ ጥንካሬዎችን ለማስቀጠል፣ ዝቅተኛ አፈጻጸም ላይ በቀጣይ ቀሪ መቶ ቀናት ለማሻሻል በትኩረት ለመስራትና ትኩረት በሚደረግባቸው ጉዳዮች ላይ ለመምከር የተዘጋጀ መድረክ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
ባለፉት ዘጠኝ ወራት በኦንላይን ንግድ ምዝገባና ፊቃድ አሰጣጥ፣ የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት የሰንበት ገበያዎችን ተደራሽ ማድረግ፣ የሸማቶች መብት ጥበቃ እንዲቋቋሙ መደረጉ፣ የነዳጅ ሪፎርም ስራዎች፣ የገቢና ወጪ ምርቶች የጥራት ቁጥጥርና የጥራት መሰረተ ልማት ፕሮጀክት ግንባታ አበረታች ውጤቶች ከተመዘገበባቸው ዘርፎች መክከል ተጠቃሾች መሆናቸውን የገለጹት ሚኒስትሩ ህገ ወጥ ንግድና የኮንትሮባንድ ፣የመሰረታዊ የሸቀጦች ሥርጭት ሥርዓትን ማዘመን፣ ቅንጅታዊ አሰራሮችን ማጠናከርና የንግድ ስራን ማዘመን፣ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች መሆናቸውን ሚኒስትሩ አክለዋል፡፡
በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ክትትል የሚደረግባት የጥራጥሬና ቅባት እህሎች ወጪ ንግድ ላይ የተገኝውን ውጤት ፣ በወጪ ንግድ ፕሮሞሽን ላይ የተሰሩ ስራዎችን ማጠናከር ይገባል ያሉት ደግሞ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ካሳሁን ጎፌ ለወጪ ንግድ እንቅፋት ሆኖ የሚገኝውን ኮንትሮባንድን ለመከላከል ከሚመለከታቸው አካላት ጋር የተቀናጀ ስራ ተጠናክሮ ሊሰራ ይገባል ሲሉ አመላክተዋል።
በውይይቱም የዘጠኝ ወሩ እቅድ አፈጻጸም በዝርዝር ቀርቦ አስተያየት ተሰቷል ፡፡