የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ካሳሁን ጎፌ የጃፓን ልዑካንን በቢሮአቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ካሳሁን ጎፌ የጃፓን ልዑካንን በቢሮአቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡ ====================== አዲስ አበባ 23/09/2016ዓ.ም (ንቀትሚ) የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ካሳሁን ጎፌ በጃፖን የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ዳባ ደበሌ በተገኙበት ከጃፖን የባለሀብቶች ልዑካን ጋር በሁለቱ ሀገራት የንግድ እና ኢንቨስትመንት ግንኙነት በሚያጠናከርበት ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡ የሁለቱ ሀገራት የንግድ ግንኙነትን ለረጅም ጊዜያት የዘለቀ መሆኑን የገለጹት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ካሳሁን ጎፌ ሀገራችን በአለም አቀፍ ንግድ ላይ ያላትን ተሳትፎና ተወዳዳሪነት ለማሳደግ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ ሚኒስተር ዴኤታው አክለውም የወጪ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ በተለያዩ ሴክተሮች ላይ እንዲሳተፉ የተፈቀደበት ወቅት በመሆኑ የጃፖን ባለሀብቶች በሀገራችን ኢንቨስት እንዲያደርጉም ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡ በጃፖን የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ዳባ ደበሌ በበኩላቸው ኢትዮጵያ በፈጣን የኢኮኖሚ እድገት ላይ የምትገኝ መሆኑን ገልፀው የጃፖን ባለሃብቶች በሀገራችንን እምቅ የንግድና ኢንቨስትመንት እድሎች ላይ ተሳትፎ እንዲያደርጉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ የልዑካኑ ተሳታፊዎች በሀገራችን የንግድ እና የኢንቨስትመንት ዘርፎች ላይ የመሳተፍ ፍላጎት እንዳላቸውም ገልፀዋል፡፡ የልዑካን ቡድኑ በሚኒስትር መስሪያ ቤቱ በመጠናቀቅ ላይ የሚገኘውን የወጪ ንግድ ምርቶች ማሳያ ቋሚ የኤግዚቢሽን ማዕከልን ጎብኝተዋል፡፡

Share this Post