========================
አዲስ አበባ 30/09/2016ዓ.ም (ንቀትሚ) የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የንግድ ትስስርና ወጪ ንግድ ፕሮሞሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ካሳሁን ጎፌ ከዓለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት(IOM) ልኡካን ጋር የጠረፍ ንግድን ማሳለጥ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ተወያዩ፡፡
ኢትዮጵያ በምትዋሰንባቸው ሀገራት ጠረፍ አካባቢ የሚካሄደውን የጠረፍ ንግድ ህጋዊ ስርዓት በማበጀት የወጪ ንግዱን ሊያበረታታ በሚችል መልኩ እንዲካሄድ ለማስቻል በርካታ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ከጂቡቲ፣ ከሱዳን፣ ከደቡብ ሱዳን እና ከኬንያ ጋር የጠረፍ ንግድ የሚካሄድባቸውን መስፈርቶችና ቅድመ ሁኔታዎች መዘጋጀታወቸውን የገለጹት ሚኒስትር ዴኤታው በተለይም ከኬንያ ጋር የሚኖረውን የጠረፍ ንግድ ስምምነት አስመልክቶ የሚቀሩ ጉዳዮችን ከ IOM ጋር በመተባበር በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ ዝግጁ ነን ብለዋል፡፡
በውይይቱ ወቅት በቀጣይ በኢትዮጰያ እና በጎረቤት ሀገራት ጋር የሚካሄደውን የጠረፍ ንግድ ለማጠናከርና ለማሳለጥ በሚቻልባቸው ስትራቴጂክ ጉዳዮች ዙሪያ በጋራ ለመስራት ከስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡