"የኢትዮጵያን ይግዙ 🇪🇹!" ግዙፍ የንግድ ባዛር እና ኤግዚቢሽን እየተካሄደ ነው። "የኢትዮጵያን ይግዙ" ጽንሰሀሳብ ከባዛር እና ኤግዚቢሽንም የሚሻገር ከፍ ያለ ጉዳይ በመሆኑ የሁሉንም ባለድርሻ አካላት ርብርብ ይጠይቃል። የሀገር ውስጥ ሁለንተናዊ የንግድ ስርአታችንን ስርኣት ማስያዝ እና ዘመኑን በዋጀ አግባብ መምራት ማለት... ያን ማለት ብቻ አይደለም። ከዚህ የሚልቅ - ከዚህም የሚርቅ አንድምታ ያለው ጉዳይ ነው። ብዙው ነገር አይን እና አፍንጫ በሆነበት እና አንዱ ሲነካ ሌላው በሚያለቅስበት የንግድ ስርአት ውስጥ እንደመኖራችን መጠን የሀገር ውስጥ ንግዳችን ሲሳለጥ እና ከኢአመክንዮአዊነት ሲጸዳ ለአጠቃላዩ የብልጽግና ጉዟችን ምንዳ እንደሚሆን እሙን ነው።
የኢትዮጵያን ይግዙ!!!
መጥተው ይጎብኙ ቦታው የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ዋናው መስሪያቤት ህንፃ 1ኛ ፎቅ ላይ ከመገናኛ ወደ ሲኤምሲ በሚወስደው መንገድ ከሴንቸሪ ሞል አጠገብ