የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮችና ሰራተኞች “የኢትዮጵያን ይግዙ” ልዩ የንግድ ሳምንት ኢግዚቪሽንና ባዛር ጎበኙ፡፡
================
አዲስ አበባ ነሀሴ 22 /2016 ዓ.ም (ንቀትሚ) በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ፍሬህይወት አበበ የተመራው የተቋሙ አመራርና ሰራተኞች በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የተዘጋጀውን በአይነቱ ልዩ የሆነውን ቋሚ የውጪ ምርቶች ማሳያ ማእከልንና የግብርናና የኢንዱስትሪ ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ ለህብረተሰቡ የቀረበበትን ኢግዚቪሸን ጎብኝተዋል፡፡
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከነሀሴ 19-23/2016 ዓ.ም ድረስ የኢትዮጵያን ይግዙ በሚል መሪ ቃል ልዩ የንግድ ሳምንት ኢግዚቪሽንና ባዛር ያዘጋጀ መሆኑና በተለያዩ የመንግስትና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት አመራርና ሰራተኞ እንዲሁም ልዩ ልዩ የህብተሰብ ክፍሎች እየተጎበኘ መሆኑ ይታወቃል፡፡
ልዩ የንግድ ሳምንት ኢግዚቪሽንና ባዛሩን ከጎበኙ የተቋማት አመራርና ሰራተኞች መካከል፡
የኢትዮጵያ የጥራት ሽልማት ድርጅት አመራርና ሰራተኞች
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አመራርና ሰራተኞች
የአዲስ አበባ ዪኒቨርሲቲ( የዴቬሎፕመንት ስቴዲስ አመራሮች መምህራንና ባለሙያዎች ይገኙበታል፡፡
የኢትዮጵያን ይግዙ ልዩ የንግድ ሳምንት በነገው እለት በንግድ ሴክተሩ የጎላ አስተዋፅኦ ላበረከቱ ተቋማትና ግለሰቦች የእውቅና እና ሽልማት ስነ ስርዓት በማካሄድ ይጠናቀቃል፡፡